የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች፣ ሃሳቦችዎን በቃላት አውቶቡስ ላይ፣ በኦንላየን፣ እና በማህበረሰብዎ ውስጥ ለማካፈል እድል እንዲኖርዎት ግጥምዎን ያስገቡ።

ከተለያዩ ባለቅኔዎች የተወጣጣው መራጭ ጓድ በኦንላየን የሚወጡ 365 ግጥሞችን ይመርጣል፣ ይህም መገናኛውን ወደ
ግጥም መድረክ የሚቀይረው ሲሆን ለአንድ ዓመት በየቀኑ አንድ ግጥም ያቀርባል። በኦንላየን እንዲታተሙ ከሚመረጡት ግጥሞች መካከል፣ ከፊሎቹ በኪንግ ካውንቲ ሜትሮና በሳውንድ ትራንዚት አውቶቡሶች ላይ፣ በባቡሮች፣ እና በመናኸሪያ ጣቢያዎች እንዲታዩ በ 2017 ውስጥ ይለጠፋሉ። ግጥሞቹ በአማርኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በቻይንኛ፣ በፑንጃቢ፣ በስፓኛ፣ በትሊንጊት፣ በቬትናምኛ፣ በሩሲያኛ እና በሱማልኛ ተጽፈው ይለጠፋሉ።

እስከ መስከረም 30, 2016፣ 11:59 ከሰዓት ድረስ፣ በፓስፊክ ሰዓት አቆጣጠር፣ የሚደርሱ ብቁ የሚሆኑ ግጥሞች ሁሉ ይጠናሉ።


ግጥሞቹን እንዴት እንደሚያስገቡ

  • “የውሃ አካልዎ” ከሚለው አርእስት ጋር የሚዛመድ ግጥም በ 50 ቃላት ወይም ከዚያ ባነሱ ቃላት፣ አርእስቱን ሳይጨምር፣ ይጻፉ።
  • በግጥም ማስገቢያው ቅጽ ለመጀመር ከዚህ በታች የሚገኘውን መገናኛ ይከተሉ።
  • ግጥም በማስገቢያ ቅጽዎ ላይ፣ ግጥምዎ ሲታተም እንዲኖረው በሚፈልጉት መልክ አድርገው ግጥሙን ይጻፉ።
  • የሚያስገቡበት ቅጽ ትክክል ለመሆኑ በድጋሚ ይመልከቱ። አንዴ ካስገቡ በኋላ ያስገቡትን ዳግመኛ ለማየት ወይም ለማረም አይችሉም።
  • ለመጀመር፣ ግጥምዎን የጻፉበትን ቋንቋ ይምረጡና ከዚያም የማስገቢያ ቅጽ (SUBMISSION FORM) ምልክቱ ላይ ጠቅ ያድርጉ፥
Select a language
  • English
  • አማርኛ

መመሪያዎቹ።

  • ለእያንዳንዱ የኪንግ ካውንቲ ነዋሪ አንድ ግጥም ብቻ።
  • ግጥሞቹ በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በፑንጃቢ፣ በሩሲያኛ፣ በሱማልኛ፣ በስፓኛ፣ በትሊንጊት (በእንግሊዘኛ ሲቀርብ)፣ እና በቬትናምኛ ቋንቋዎች ሊቀርቡ ይችላሉ።
  • ከእንግሊዘኛ በቀር በሌሎች ቋንቋዎች የሚቀርቡ ግጥሞች፣ የእንግሊዘኛ ትርጉም መጨመር አለባቸው። በእንግሊዘኛ ተተርጉሞ የሚቀርበው ግጥም ለአጥኚው ጓድ ማመሳከሪያ እንዲሆን ብቻ ነው። ግጥምዎ ከተመረጠ፣ ከመታተሙ በፊት በባለሙያ እንዲተረጎም ይደረጋል።
  • ግጥሞቹ የራስዎ ኦሪጅናል ጽሁፎች መሆን አለባቸው፣ እንዲሁም አርእስቱ ሳይቆጠር የ 50 ቃላት ወይም ያነሰ መሆን አለባቸው።
  • ደራሲዎች ለግጥማቸው ያላቸው ሕጋዊ መብት የተጠበቀ ነው፣ ግን የተመረጡትን ግጥሞች ለአውቶቡስ ላይ ግጥም (Poetry on Buses) ለጥፎ የማሳየት መብት ይሰጡታል።
  • ግጥሞቹ እስከ መስከረም 30, 2016፣ 11:59 ከሰዓት ድረስ፣ በፓስፊክ ሰዓት አቆጣጠር፣ መግባት አለባቸው።

የምርጫው ሂደት

  • ግጥሞቹ የሚመረጡበት መሠረት፥
    • “የውሃ አካልዎ” ከሚለው አርእርስት ጋር ባላቸው ዝምድና
    • በኪነ ጥበባዊ ችሎታ
    • በአውቶቡስ እና በኦንላየን ለማውጣት ተገቢ እንደመሆናቸው
    • መመሪያዎችን በማክበራቸው
  • ግጥሞቹ የሚከተሉትን በሚጨምሩ መደቦች መሠረት ይገመገማሉ፣ “ወጣት ባለቅኔዎች” (ከ 18 እድሜ በታች)፣ ለ 2016-17 “ትኩረት የተደረገባቸው ቋንቋዎች” (አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ ፑንጃቢ፣ ስፓኛ፣ እና ትሊንጊት) እና “አጠቃላይ የሕዝብ ባለቅኔዎች።”
  • ሁሉም ባለቅኔዎች እስከ 2017 መጀመሪያ ጊዜ ድረስ ስለ ምርጫው ሂደት ውጤቶች ማስታወቂያ ይሰጣቸዋል። ለኦንላየን እግዝቢት እንዲወጡ ከሚመረጡት ግጥሞች መካከል፣ ከፊሎቹ በኪንግ ካውንቲ ሜትሮና በሳውንድ ትራንዚት አውቶቡሶች ላይ፣ በባቡሮች፣ እና በመናኸሪያ ጣቢያዎች ወዘተ እንዲታዩ በ 2017 ውስጥ ይለጠፋሉ።