August 27th
ሲተንም ሽቅብ ወደ ላይ
ሲዘንብም ቁልቁል ከሰማይ
ጠጥሮም እንደ በረዶ
ከሰማየ ሰማያት ወርዶሳንተዋወቅ አዛምዶን
ተቆራኝተናል ተላምደን
እናም………..
እንጠጣ ቀድተን ከጓዳ
ውስጣችን አጥቦ እያፀዳ
ከደማችን ጋራ ይዘነቅ
የኑረትን ሃይል እንሰንቅ
ከባህር ከወንዝ ከሐይቅ
እኛነት ሄዶ ሲዘፈቅ
ከምንጩ በመንፈስ ብንጠልቅ
ነፍሳችን ነፍስ እንዲኖራት
ካለ ውሃ ከቶ ማን አላት?
ሲተንም ሽቅብ ወደ ላይ
ሲዘንብም ቁልቁል ከሰማይ
ጠጥሮም እንደ በረዶ
ከሰማየ ሰማያት ወርዶሳንተዋወቅ አዛምዶን
ተቆራኝተናል ተላምደን
እናም………..
እንጠጣ ቀድተን ከጓዳ
ውስጣችን አጥቦ እያፀዳ
ከደማችን ጋራ ይዘነቅ
የኑረትን ሃይል እንሰንቅ
ከባህር ከወንዝ ከሐይቅ
እኛነት ሄዶ ሲዘፈቅ
ከምንጩ በመንፈስ ብንጠልቅ
ነፍሳችን ነፍስ እንዲኖራት
ካለ ውሃ ከቶ ማን አላት?
When water evaporates
It goes back to the sky.
When it rains
It comes down from the sky.
It also makes ice and falls down.
Because it is water’s nature to be everywhere
We, people, share the same experience and common culture.
Let’s drink it in our home
Let’s clean our insides
And flow it in to our blood
Let’s get the power to live
And immerse ourselves in the sea and lake
With a good spirit intake.
For our soul to have soul and breathe better
What is more important than our water?