February 27th
ግራ፡እሚያጋባ፡ ነው፡ ዝም፡ ብሎ፡ ላየው፣
ሰው፡እንዴት፡ያፈሳል፡ ውሃ፡ እየጠማው፣
ብላችሁ፡ አትፍረዱ፡ ግራ ለገባው።
ካአይኑ፡ የሚፈሰው፡ ውሃ፡ ልቡ፡ ተንዶ፡ነው፣
ወዶ፡ አይምሰላችሁ፡እሮሮው፡በዝቶ፡ ነው።
ታዲያ፡ይህን፡ ውሃ፡ እንባ፡ የሚሉት፣
ማጠራቀም፡ ብችል፡ ግንብ፡ ብሠራለት፣
ከሌለው፡ ሳልቀማ፡ ሳልሰበስብ፡ አስራት፣
ታይቶ፡የማይታወቅ፡ ይሆናል፡ ጅረት።
ግራ፡እሚያጋባ፡ ነው፡ ዝም፡ ብሎ፡ ላየው፣
ሰው፡እንዴት፡ያፈሳል፡ ውሃ፡ እየጠማው፣
ብላችሁ፡ አትፍረዱ፡ ግራ ለገባው።
ካአይኑ፡ የሚፈሰው፡ ውሃ፡ ልቡ፡ ተንዶ፡ነው፣
ወዶ፡ አይምሰላችሁ፡እሮሮው፡በዝቶ፡ ነው።
ታዲያ፡ይህን፡ ውሃ፡ እንባ፡ የሚሉት፣
ማጠራቀም፡ ብችል፡ ግንብ፡ ብሠራለት፣
ከሌለው፡ ሳልቀማ፡ ሳልሰበስብ፡ አስራት፣
ታይቶ፡የማይታወቅ፡ ይሆናል፡ ጅረት።
It is confusing to see
A man dropping water from his eyes
While he is thirsty.
But, please don’t judge him
For not controlling it
As he feels empty
Because of his broken heart.
If I collected his tears
And were able to build a dam
Without asking money from no one
I would create an amazing stream.