POET OF THE WEEK
Samson Yirsaw Getenet
Week of January 15
አምና እንዳሳለፍነው….ከባህሩ ዳርቻ
ዛሬም በቀጠሮ ….ሄድኩና ለብቻ
ውሃን አገኘሁት…ሚስጥሬን ላጋራ
ያለኝን ሳላስቀር ….ሁሉንም ላወራ::
ድሮ የማውቀው ውሃ.…አሁን ግን ደፍርሷል
መልኩ ተጎሳቁሎ….ውበቱ ገርጥቷል
ለምን እንደሆነ …ምክንያቱን ስጠይቅ
እንባ እያነቀው….አጫወተኝ በጭንቅ
እንዲህ ደም ግባቱ … ወዘናው የጠፋው
ውስጡ ተበክሎ…..ዘይት የሚተፋው
በሰው ልጆች ጥፋት …መሆኑን ተረዳው::
አምና እንዳሳለፍነው….ከባህሩ ዳርቻ
ዛሬም በቀጠሮ ….ሄድኩና ለብቻ
ውሃን አገኘሁት…ሚስጥሬን ላጋራ
ያለኝን ሳላስቀር ….ሁሉንም ላወራ::
ድሮ የማውቀው ውሃ.…አሁን ግን ደፍርሷል
መልኩ ተጎሳቁሎ….ውበቱ ገርጥቷል
ለምን እንደሆነ …ምክንያቱን ስጠይቅ
እንባ እያነቀው….አጫወተኝ በጭንቅ
እንዲህ ደም ግባቱ … ወዘናው የጠፋው
ውስጡ ተበክሎ…..ዘይት የሚተፋው
በሰው ልጆች ጥፋት …መሆኑን ተረዳው::
As I used to do it before
I went to the sea shore…
And played with water.
And started sharing my secret
Being ready to enjoy at my best.
But the water was not as I expected…
It looked weak and sad
because of the pollution caused by man.
FIRST POEM I was 8. The poem is in the form of asking my mother how I was born. It was left with a question mark at the end.
FAVORITE POETRY FORM Short rhyme poems.
DEAREST BODY OF WATER Awash River (in Ethiopia).